መታሰቢያነቱ የራሳችሁን ዓለም በመተው በልጃችሁ ዓለም ለምትኖሩ፣ የልጃችሁ ጥቂት ለውጥ ለነፍሳችሁ ደስታ ለሆነላችሁ፣ የነገን ብርሃን በተስፋ በመጠበቅ የዛሬን ፈተና እንደ ድልድይ ለቆጠራችሁ፣ ባለመሰልቸት አይሆንምን በይሆናል ለመቀየር ለምትተጉ፣ ውድ ወላጆች ይሁን እናንተ ጨለማውን ማጥፊያ ብርሃን ናችሁና!!!
USD $10
ማጠቃለያ
በዚህ ታሪክ ብዙ ወላጆች ብዙ እውቀት እንደሚያገኙበት እሙን ነው፡፡ እሱም ብቻ አይደለም፣ የልጃቸውን ችግር ባለማወቅ ለሚንገላቱም ትልቅ የእውቀት ምንጭ ነው፣ ምን እናድርግ ለሚሉ መንገድ ይመራል፣ በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ ወላጆች ታሪክ ብዙ ነገር ነው፣ በእውት ብርሃን እንድንመላለስ ከማድረጉም ባሻገር ተስፋ ለሚቆረጡ ወላጆች ተስፋ የሚቀጥል ነው፣ በማማረር ላሉ ወላጆችም ይህም አለ እንዴት ብለው ልጃቸው ላይ ለመስራት እንዲተጉ ምርኩዝም የሚሆን ነው፣ አዎ ይህ መጽሐፍ ስታነቡ በየታሪኮች ያሉ ልምዶች ምን ያክል እንደሚያስጨንቁ፣ መገመት አያዳግትም፡፡ አንዳንድ ወላጆች ባለማወቅ ችግር ሲገጥማቸው አይታችሁል፣ አንዳንዶች ደግሞ የደረሰውን ችግር እንኳን እያወቁ ላለመቀበል ምን ያክል እራሳቸውን እንደሚሸውዱ መረዳት ችላችሁል፣ ነገር ግን አንድ እውነት ደግሞ አለ፣ ያለውን ችግር ከመሸሽ ይልቅ መፍትሄ ላይ ኩረት በማድረግ ልጃቸውላ ለውጥ ያመቱ እናቶችንም ታሪክ አንብባችሁል፡፡
ታዲያ ይህ ሁሉ ለእናንተ ነው፣ ድካማችሁን ለመቀነስ፣ ታስቦ የተዘጋጀው፣ ወላጆችንም ሌሎች ወላጆች ከእኛ ይማሩ እኛ ደረሰብን አይድረስባቸው በማለት ታሪኩን በጹሕፍ እንዲሰፍ ያደረጉት፣ በዚህም እነዚህ ታሪካቸውን ሳይሰስቱ ላበረከቱ ወላጆች የምስጋ ቃል እንኳን ያንሳቸዋል፣ ግን ሌላ የምንለው ባለመኖሩ እናመሰግናለን ሌላው በእናንተ ታሪክ እንዲማር ድርሻችሁን ተወጥታችሁዋልና፡፡