Sqrindle
Mulsha Artist

Mulsha Artist

About Mulsha Artist

ህልም ብቻ ያልሆነ እውነት …

አቀበት ያልፈተነው፣ በረሃ ያልረታው፣ ውሃ ጥም ያላስቀረው የስደት ግብግብ ። ባህርን ረቶ ሞትን ተጋፍጦ ድል የነሳ ማንነት ። ሻካራነት ያልፈተነው ድንቅ መዳፍ መስራት ማይታክተው ታምራዊ ጉልበት ድካም የማይረታ ፣እንቅልፍ ማያሸንፈው ፈጣሪ ዓይምሮ ከራስ አልፎ ለሌላው የመትረፍ የሴትነት እልህና የይቻላል መንፈስ አወ እኔ "ስደት ሕልሜን ያልቀማኝ ሕልሜም ደግሞ የተሰደትኩበትን አላማ ያላስረሳኝ" ጠንካራ ሴት ነኝ ።

የስደቴ አላማ :-

የቤታችን የመጀመራ ልጅ እንደ መሆኔ መጠን የእሕቴ እና የወንድሞቸ ሀላፊነት ስላለብን ለእነሱ የነገ ተስፋ ስንቅ ለመቋጠር ሲባል ድሕነትን መርታት አማራጭ የሌለው የውዴታ ግዴታየ ስለሆነ ከአስከፊው የሞት ጥላ ታግየ የሕይወት አስከፊ ገፅታወችን ተዋግቸ የኑሮን ዳገት መውጣት ችያለሁ ። እናም የሚማሩትን እስተምሬ እንዲሁም ማግባት የሚሹትንም ድሬ ኩያለሁ።

ሕልምን ማሳካት:-

ሰው በስደት ህይወት ውስጥ ሆኖ ህልምን ማሳካት ብቻ ሳይሆን ከራስ አልፎ ለሀገር መትረፍና ሌት ተቀን በርሃብና በበሽታ የሚሰቃይን ወገን መርዳት ይቻላል ።

በቀን አድካሚ የቤት ስራዎችን እየሰራሁ ውዬ፣ ለሊት እንቅልፌን መስዋዕት በማድረግ (በቀን የሁለት ሰዓት እንቅልፍ ብቻ በመተኛት) ከዚህ በፊት ሦስት መጻሕፍትን ማሳተም ችያለሁ።

ታዲያ የበለጠ አስገራሚው ነገር ግን፣ በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ተጽፈው የወጡት የመጻሕፍቶቼ የሽያጭ ገቢ ሙሉ በሙሉ (100%) ለበጎ አድራጎት እንዲውሉ ማድረጌ ነው።
በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ መጻሕፍቶቿን ሙሉ በሙሉ ለሕክምና እርዳታ በመለገስ የመጀመሪያዋ ደራሲ ለመሆን በቅቻለሁ እንዲሁም የተለያዩ ደራሲያን በፐርስንት ለተለያዩ በጎ እድራጎቶች እየተለመደ መጥቷል ለዚሕ መንገድ መሆን የቻልኩ ይመስለኛል።

የሥራዎቼና የለጋሽነት አሻራዎቼ ዝርዝር፦
"ስደተኛ ስንኞች" (የግጥም መድብል - 2010 ዓ.ም)፦ ገቢው ለጌርጌሲኖ አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ውሏል።

ከጓደኛየ ሂዊ ጌታቸው ጋር የጋራ ድርሰታችን "ከራስ ሽሽት" (ልብ-ወለድ - 2013 ዓ.ም)፦ ገቢው ለሕፃናት የልብ ሕሙማን ማዕከል ተሰጥቷል።

"ጣፋጭ ሲቃ" (ልብ-ወለድ - 2016 ዓ.ም)፦ ገቢው ተስፋ አዲስ ለሕፃናት ካንሰር ሕሙማን ማዕከል ድጋፍ ሆኗል።

አሁን ላይ ብቻ 2018/ዓ/ም " "መነን" የተሰኘ ፊልም እና
" ነዋዥ" የተሰኘ
በ 14 ዓምት የስደት ሕይወት እኔ እና መስሎቸ የኖርነውን ይሚዳስስ
"የተሸነፈ ደም " ልበወለድ መፅሐፍ
"የሕወት ታሪክ"
ቤተ እስራኤላዊ ታዋቂው እና ተወዳጁ ሁለገብ አርቲስት ሰለሞን መርሻን የሚዳስስ።
ስወስት አዳዲስ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ላይ እገኛለሁ።

ይህ ታሪኬ በስደት ላሉ ኢትዮጵያውያን ብርታት፣ ለደራሲያን ደግሞ አርአያ ይሆናል ብዬ በማመን ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ለመስጠትና በስልክም ሆነ በኢንተርኔት ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ ለሚፈልገኝ አካላት ሁሉ ልምድና የህይወት ተሞክሮዬን ለማጋራትዝግጁ ነመሆኔን በደስታ እገልፃለሁ።
ኑ መጪዋን ኢትዮጵያ አብረን እንገንባ።

ደራሲና ገጣሚ ሙሉ ደርቤ (አባ አብርሃ)

Books By Mulsha Artist